የፌደራል ገቢ ግብር አዋጅ።
የአዋጁ መግቢያ
የአገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት ከደረሰበት ደረጃ ጋር የተጣጣመ እና የኢኮኖሚውን ዕድገት የሚያግዝ ዘመናዊና ቀልጣፋ የግብር ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤
የግብር አከፋፈሉ ሥርዓት ፍትሃዊነት ያለው እንዲሆን እና ግብር የማይከፈልባቸው ገቢዎች በግብር መረብ ውስጥ እንዲገቡ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 55(1) እና (01) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
